Monday, February 27, 2017

እያስፈራሩ መለማመጥ፤እየተለማመጡ መብለጥለጥ( http://www.finote.org )

የፍኖተ ራዲዮ ወቅታዊ ሀተታ


እያስፈራሩ    መለማመጥ፤                                      እየተለማመጡ  መብለጥለጥ

ፈሪ፤ ሁለት ዶላዎች ሸክሞ  ይዞራል  ። ይኽንን  የሚያደርገው   ሁለት  አማራጮችን እጠቀማለሁ ከሚል ምኞት ነው።  በአንዱ እያስፈራራሁ ፤ በሌላው  እከላከላለሁ ከሚል ዕሳቤ የመጣና ቆርጠኝነትን ካጣ ልብ የሚመነጭ ወኔ -ቢስነት ነው ። ፈሪ ካገኘሁ፤  አባርርበታለሁ። ደፋር ከመጣብኝም እከላክልበታለሁ  የሚል ስልት የሚያዋጣ ይመስለዋል።  ሁለት ልብ ይዞ መጓዝ፤ ለውጤት አያበቃም  ። " በሁለት ባላዎች ተሰቀል፤ አንዱ ሲሰበር፤ በሌላው ተንጠልጠል " ከሚለው ቢሂል የተገኘ አስተምህሮ  ይመስላል ። እጅ ሳይሰጡ ማምለጥ፤ አምልጦም ሙያ መስራቱ ሳይሆን ሲቀር፤ ተርበትብቶ  በጠላት እጅ  እየወደቁ ፤ በመቆለጭለጭ ፤ የነፍስ አድን መለማመጥንና መቅበዝበዝን ያመጣል።  ተርበባችና ተቅበዝባች ልብ ያለው ደግሞ ለፓለቲካ ትግልም ሆነ ለጦር ሜዳ ፍልሚያ ችንፋትን እንጅ፤ ድልን አይጎናፀፍም ። ውጤቱ፤  የታዛቢ  መሳለቂያ ሆኖ  መቅረት  ይሆናል     በዚህ ከስተት  ወስጥ  የሚገኝ  ሁሉ    ከሕዝብ   መሳቂያ- መሳለቂ  የሚወጣ   እየመሰለው " ወይ በምድር ያለ ሰው ?  "  የሚል ጥያቄ አዝጋጅቶ ይጠብቃል ።  ከውርደት- ከሀፍረት ነፃ የሚሆን እየመሰለው !
በማነኛው ኅብረተሰብ ውስጥ ፤ ልዕለ-ኃያል ሕዝብ ነው። ሕዝብ ፤ የታሪክ ፤ የባኅል፤ የፖለቲካ፤ የምጣኔ ሀብት ፤ ሁሉ መሠረትና ምንጭ በመሆኑ፤ ፈርጀ- ብዙ ኃይል አለው። የማይገደብ፤ የማይበገር፤ የማይደራደር ሥልጣን የራሱ ብቻ ነው። የማይገሰስ፤ የማይደፈር፤ ነፃነትና መብት የራሱ የግሉ ነው።  ይኽንን ልዕለ-ኃይል፤ በኅይል ለብዙ ጊዜ መግዛት አይቻልም ።  ልዕለ-ኃያሉ ሕዝብ ፤ ዕምቅና ተንቀሳቃሽ ኅይሉን አስተበብሮ ያምጻል ። አመፁም እሳተ ገሞራ ሆኖ እንደ መንጥር እሣት ያቃጥላል። አምባገነን ገዥዎቹን ያጠፋል  ። የዶግ-አመድ አድርጎ የበታትናል ። ይኽን ዘመን ተሻጋሪ የሆነውን ሀቅ ሳይረዱ፤ የመንግሥት ሥልጣን ላይ መቀመጥ፤ እሣት መጨበጥ ነው። እያስፈራሩ መግዛትም ሆነ እየተለማመጡ የሥልጣን ዘመንን  ማራዘም፤ ጊዜ ያለፈበት፤ ከጉለተኛው ሥረዓተ -ማኅበር ጋር ወደ ታሪክ ማኅደር ከተከተተ ግማሽ - ምዕተ ዓመት አስቆጥሯል ፡፡
በሃያ-አንደኛው ክፍለ-ዘመን ላይ ያለቸው ሀገራችን፤ አሁንም፤ ከአምባገነኖች መዳፍ ለትላቀቅ አልቻለችም። ብዙ ጊዜ ነፃ ለመውጥት ሞክራ ሞክራም አልተሳካላትም  ።የለውጥ እስትንፋስ አገኘሁ በምትልበት ወቅትም ቢሆን፤ እሳተ-በላ አምባገንን እየመጣባት  ፍዳውን ታያለች።  አዲሱ አምባገነን አሮጌውን ሲተካው፤ የባሰ እንጅ የተሻለ ሆኖ አይገኘም ። ለዚህ  ዋና ምክንያት፤ የሕዝብን ልዕለ-ኃያልነት ካለማወቅ ወይም ከመናቅ የሚመጣ   ትዕቢትና ድንቁርና ነው። ትዕቢትና ድንቁርና፤ ድርና ማግ ሆነው ከመጡ፤ ሀገር አጥፍተው፤ እነርሱም ይጠፋሉ። ይኽ ከስተት በቅርቡ የሀገራችን ታሪክ ተመዝግቧል ። የደርግን ፍጻሜ የጤኗል ! 
 ደርግን የተካው ቡድን ፤ የአንድ ብሄርን ጥቅም ለማስጠበቅ ተደራጅቶና ታጥቆ በመምጣቱ፤ አሁን ከሚሰራው የተለየ ለመላው ሀገሪቱ የሚጠቅም ጉዳይ ያሟላል ተብሎ አልተጠበቀም ነበርና ያን መፈፀሙ ሊያስደንቅ አልቻለም  ። ኢትዮጵያን እንደ ጥገት ላም እያለበ፤ ለመበዝበዝ የመጣ ስለነበር፤  የተነሳበትን ዓላማ ግብ ከመምታት ያለፈ ነገር ለማከናወን ጉዳዩ አይደለም  ። ግቡን ለማስፈፀም  እንዲሚመቸው ደግሞ፤እጅግ  መሰሪ  የሆነ  የአምባገንን አገዘዝ በመዘርጋቱ ነው ። ከደርግ የተለየ አምባገነን የሚያደርገውም፤ በዘር የተደራጀ መሆኑ ነው፡፡ ሀገሪቱም በታሪኳ፤በዘር  የተማከለ አገዛዝ ስር ስትወድቅ የመጀመሪያዋ ነበር።  " ሀገር ሲያረጅ ፤ ጃርት ያበቅላል ። " ሆኖባት ነው መሰል፤  ጥንታዊቷ ኢትዮጵያ ሀገራችን  ይኽው ዛሬ የጃርቶች  መጫዎቻ ሆናለች  ! 
 የወቅቱ  አምባገነን አገዛዝ፤ ከሌሎቹ አጋዛዞች የሚለየው፤ ያደረጃጀቱ፤ ያወቃቀሩና የተግባር አፈፃጸሙ፤ ፀረ ኢትዮጵያ መሆን ብቻ ሳይሆን፤ ከሀገሪቱ ባላንጣዎች በኩል፤  ያልተቋረጠና ያልተቆጠበ ሁል-አቀፍ ርዳታ ማግኘቱም ጭምር ነው ።  ይኽ ዘረኛ  ቡድን፤ ከርሱ በፊት ከነበሩት ሁለት አጋዛዞች እጅግ በበለጠ፤ የውጭ ርዳታን ያገኛል  ። ይኽ ደግሞ ያለምክንያት አይደለም። 
ወያኔ፤ ዛሬ የሀገሪቱን ውስጠ -ምሥጥር  ሁሉ  ልባዕዳኑ አስረግቧቸዋል  ። ብሄራዊ ሀብቷን እንደልባቸው እየዘረፉ እንዲወስዱ አመቻችቶ ሰጥቷቸዋል     የጥቅም አባሪ -ተባባሪ የሆነ ኃይል ደግሞ፤ ሲጠሩት አቤት  ሲልኩት ወዴት የሚል አግልጋይ ማግኘቱ አይቀርም። ምን ጊዜም ቢሆን ባዕዳን፤ የሚጠሉት ነገር ቢኖር ፤ ሀገር-ወዳድ የሆነን ቡድን ስለሆነ፤  ሀገሩንና ሕዝቡን የከዳውን  ፤የሀገር ውስጥ ባንዳ ሁሉ፤ እንደ በኸር ልጅ አሽሞንሙነው ይይዙታል ።  ታዲያ፤ ወያኔን እቅፋቸው ውስጥ አስገብተው ሁለንተናዊ ድጋፍ መስጠታቸው የሚያስደንቅ አይደለም    ምን ጊዜም ቢሆን ውሻ  ላበላው ሁሉ ጭራውን እየቆላ  ይቁለጨለጫል  ። ይጮኻል ።  "ጉቦ የበላ ዳኛ ፤ የፍርድ መጋኛ " እንዲሉ፤  የባእዳኑን እጅ የላሰ ባንዳም እንዲሁ፤ የሀገር መጋኛ  መሆኑ አይቀርም ።
 በቅርብ የታሪክ ሂደት፤ የብዙ ሀገሮች ሀገር ወዳድ መሪዎች በምዕርባውያኑ ተንኮልና ሴራ  ተገድለዋል፡፡ ከሥልጣናቸው በግፍ ተበርረዋል  ።ዶ/ር ክዋሚ  ንኩርማህ  ፤ የጋናው ፕሬዝደንት፤  ፓትሪስ ሉሙባ  የጎንጎው መሪ፤ አህመድ ቤንቤላ የአልጀሪያው መሪ ፤ ከአፍሪካ አህጉር ይጠቀሳሉ። ሳልቫዶሬ አይንዴ ፤ ከደቡብ አሜሪካ በግፍ ተገድሏል ፡፡
 የዚህ ሁሉ ወንጅል ፈፃሚዎች ምዕራባውያን ናቸው ።  ሁሉም የሀገር መሪዎች በግፍ የተገደሉት ፤ ሀገራቸውንና ህዝባቸውን  ስለሚወዱ ብቻ ነበር ። ዐርበኞች ነበሩ። የየሀገራቸውን ብሄራዊ ጥቅሞች ፤ ለባዕዳን ጥቅም አሳልፈን አንሰጥም ባዮች ነበሩ ። ምዕራባውያኑ እነርሱን እያስወገዱ ፤ የራሳቸውን ታማኝ አሽከሮች በቦታቸው አስቀምጠዋል ።  ወደ ዝርዝር ጉዳዩ መግባት፤ የዚህ ሐተታ ቅድሚያ ስላይደለ፤ ብዙ ማለት አልፈለግንም ።
የዛሬይቱ ኢትዮጵያ   "መሪዎች" ፀረ ኢትዮጵያ ስለሆኑ ሀገር ወዳዶች ናቸው ተብለው አይጠረጠሩም ። ይኽ ማንነታቸው፤ የባዕዳኑን ጥቅም አስጠባቂ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል ። ይኽ ደግሞ ያልተቆጠበና ያልተቋረጠ ድጋፍ አስገኝቶላቸዋል ። ሆኖም ድጋፉና ትብብሩ እስክ ዘለቄታው የሚሄድ አይደለም ። ሁሉ የየራሱን ጥቅም እየተከታተለ ስለሚጠብቅ፤ ወለም-ዘለም የሚል ሁኔታ መፈጠሩን ሲገነዘብ፤ ወያኔን  የደገፈው ሁሉ፤ አፍንጫህን ላስ  እያለ ይከደዋል  ። ትላትና ፤ የሶቬይቱ መሪ ሚካሄል ጎርባቾቭ፤ በሚገርም ሁኔታ፤ መንግሥቱ ኃይለማርያን  እንዴት እንደከዳው የቅርብ ትዝታ ሆኗል 
 የወያኔ ቀን እየጨለመበት መምጣቱ  ምልክትም አፍጥጦ እየመጣ ነው ። ይኽንንም ወያኔዎቹ ሳይገነዘቡት የሚቆሩ አይደሉም ። ምዕራባውያን አለቆቹም፤ "አቋምክን ካላስተካክለህ፤ ያገዛዝ ስልትህን ካልቀየርክ፤  ከሕዝቡ ጋር ካልተደራደርክ፤ ሥልጣንህን የምታጣበት ጊዜ  መቃረቡን  ማወቅ አልብህ ብለውታል  ። እየዋለ እያደረ ፤ ወያኔ ከሁለት ያጣ  ጎመን እንደሚሆን ሳይረዳው  አልቀረም  ። በዚህ ምክንያት ሕዝቡን ለመለማመጥ ላይ ታች እያለ ይገኛል ።  የቻይናን ካርድ መጠቀም እችላለሁ ብሎ ራሱን ማታለሉ ግን አይቀርም ። ራሱን ማታለል የሚችል ቡድን፤ ሌላውንም ማታለል አውቅበታለሁ  እያለ ራሱን ያታልላል ። ይኽ ደግሞ ፤ የሥነአዕምሮ በሽታ ልክፍት ነው።
 ይኽ ዘረኛ ቡድን፤ የህዝቡን አመፅ አቅጣጫ ለማሳት፤ የተለያዩ ሙከራዎች በማካሄድ ላይ ይገኛል ። ሁለት ተደጋጋፊና ተፈራራቂ ዘዴዎችን ለመጠቀም እየተፍጨረጨረ ነው።  "ሲፋጅ  በመንኪያ ፤ ሲበርድ በእጅ  "ን  ታክቲክ ለመጠቀም  ይከጅላል።  እያስፈራሩ  መለማመጥ፤ እያተለማመጡ ማዘናጋት፤ እያዘናጉ ትጥቅ ማስፈታታት፤  የሕዝቡን ቆጣ ማብረድ ፤ እያበረዱ ማኮላሸት፤ እያኮላሹ ለጥ ሰጥ አድርጎ ለመግዛት፤ እየተመኘ፤ አዳዲስ እቅዶች ለማውጣት እየሞከረ ነው።   በመሆኑም ፤ ሀገሪቱን  በዚህ ዙሪያ ጥምጥም አስገብቶ ማሽከርከር፤ ተቃማሚ ነኝ የሚለውንም  እያደነዘዘ፤ ለሥልጣን እያስቋመጠ፤ በዕርጎ ባህር እንዲዋኝ  ያደርገዋል  ። በቀቢፀ-ተስፋ  ያስማልለዋል ። ድዱን አርገፎ ፤ ጥርስ የሌላው እምባጮ ያደርገዋል  ። ከዚያ በኋላ፤ ተቃዋሚዎች ነን ባዮች፤ በየኤምባሲዎቹ እያዞሩ ደጀ-ጠኝነታቸውን ይቀጥላሉ ።  ምዕራባውያኑ ደግሞ፤  ደጀ- እንዲጠኑላቸው ይፈልጋሉ ። ከደጅ ጠኞዮቹ መካከል ፤ የራሳቸውን ሰዎች ለመመልመል ፤ ያመቻቸዋልና !
ዎያኔዎቹ አሁን  ፤ ወቅቱን እያጠበቀ የሚታደስ፤ የውሃ ቅዳ- ውሃ -መልስ፤ የፕሮፓጋንዳ ታክቲክ  በመጠቀም ላይ ናቸው። በሂደት  የመጀመሪያው ሙከራ   ሲከሽፍባቸው፤  ሁለተኛውን ያስከትላሉ ። ይኽ ዘዴ ደግሞ፤ ሕዝቡን እያደነዘዙ፤ ተስፋ ለማስቆረትና ያለ ስጋት አጋዛዛቸውን ለመቀጠል ይረዳናል ብለው ያስባሉ ፡፤ ይኽ ግን ዘለቄታ አይኖረውም 
ወቅታዊው  የማስፈራራት ፤የማደንዘዝና የመለማመጥ  ጥረታቸውን ፤ ይዘው ብቅ ማለት ጀምረዋል  
1ኛ. አስቸኳይ አዋጅ አውጆ ማስፈራራት ነበር ። እርሱ አልሰራላቸውም ። የሕዝቡን አመጽ ሊገታው አልቻለም ። ወጣቱ ትውልድ አይከፉሉ መሥዋዕት እያከፈለ ጥግሉን ቀጥሏል።  ሕዝቡም በአስቸኳይ አዋጃቸው አልተደናገጠም። አልተከፋፈለም ። አዋጃቸው አንዳልሰራላቸው እነርሱ እራሳቸውም ተግንዝበውታል ።በዚህ ምክንያት አሁን ሲጨንቃጨው፤ሁለተኛውን   ዘዴ ይዘው መጡ ፦
2ኛ.  ጥልቅ  ህዳሴ- ያለተቋረጠ ግምገማ፤ የሚል ማደንዘዣና ማጭበርበሪያ አመጡ ። ስህተታችን እናርማለን የሚል የማጭበርበሪያ ፕሮፓጋንዳ ጨዋታ አሳዩ ። ሙናን መዋጋት፤  ኪራይ ሰቢን መቅጣት ፤ብለው ብቅ አሉ። እርሱም ሊሰራላቸው አልቻለም ። በግድ ወደ ሦስተኛ ሽወዳ መሄድ ነበረባቸው ። የኸውም የሀገሪቱን ካርታ እደገና መበወዝ  የሚል አስቂኝ ድራማ  ነው።
3ኛ.   ክልሎችን፤  ወደ ክፍለ ሀገር /  ጠቅላይ ግዛት እንሸንሽን  የሚል ካርታ  ለቅልቀው በተዘዋዋሪ ወርወር ያደረጉበትም ሁኔታም ነበር ። ሕዝቡ ግን፤ አንችው ትውስጅው ፤ አንችው  ታመጭው   አላቸው። የሚዙት -የሚጨብጡት  አጡ ። የሀገሪቱ መልከዐ- ምድር የተበከለው፤ በዘርና በቋንቋ  በመከፋፈሉ ስለሆነ፤ብክለቱን አያስወግደውም። የካርታ  ብወዛ፤ መሠረታዊ ችግሩን  አያጠፋውም። ወያኔያዊ የግዛት አከፋፈል ያመጣው ጠንቅ ሊወገድ የሚችለው ፤ በካርታ ብወዛና በመሬት አሸናሸን ሊሆን አይችልም ።  የችግሩ መሠረታዊ  ምክንያት  የሆነው፤ወያኔ ሲወገድ ብቻ ነው ኢትዮጵያ ሠላምና መረጋጋት የምታገኘው ። ያለዚያ ወሃ ቅዳ ውሃ መልስ ከመሆን አያልፍም    ወያኔዎቹ፤ ሦስቱ ሞከራዎች እንዳልሰሩላቸው ሲገነዘቡ፤   ወደ ሌላ አራተኛ መጭበርበሪያ ለማቅረብ ተገደዱ።  ይኽም፤ እየተወያዩ  መደራደር  የሚሉት ፤የቁማር ጨዋታ ነው።    
4ኛ.  ከተቃዋሚው ጋር  ውይይት- ድርድር  የሚባል ድራማ ደግሞ የሰሞኑ ፈሊጥ ሆኖ መጥቷል ።  " የጨነቀው ሙቅ -ያንቀውልና "ከጊዜ ወደ ጊዜ እያገመገመ የመጣውን ሕዝባዊ አመፅ መግታት ያስችለኛል ይሆናል የሚል ቀቢፀ-ተስፋን፤ ተስፋ ያደረገ  ፤ ተቃዋሚውን አፍ ለመዝጋት፤ ለመከፋፈል፤ ዕርቀ-ሠላም ሊወርድ ነው፤ ብሎ ሕዝቡ  የትግል ዓርማውን ወደ ሰገባው እንዲያስገባ ለመገፍፋት  ከሚደረግ ሙከራ አያልፍም። 
የፖለቲካ ሳይንስ  ክኅሎት አለን የሚሉ ሰዎች አንደሚሉት ፤ በመሠረቱ ፤ ጦርነትን በአቸናፊነት ለማጠናቀቅ፤አዛዦቹ በጠላት ላይ የማታለል  ችሎታውን ማሳያት አንደሚኖርባቸው ያስገነዝባሉ ።በግልባጩ ደግሞ የፖለቲካና የመንግሥት መሪዎችም ህዝብን የማታለል ችሎታ ካለን፤ እንደልብ  መግዛት አያቅተንም ብለው ራሳቸውን መደለላቸው አይቀርም ።  የዎያኔ መሪዎቹም ፤ የዚህን ወጋ-ወግ  የቃረሙ ይመስላል።  ሕዝብን  "የማታለል "  ችሎታችን ከፍተኛ ደረጃ ደርሷል ብለው  ደምድመዋል ።
ከላይ በተራ ቁጥር አንድ እስከ አራት  የተጠቅሱት ሕዝብን የማታለል ሙከራዎች ሁሉ ፤ፋይዳ ቢሶች መሆናቸው በሂደት እየታየ  ነው። የሕዝቡን አልገዛም ባይነትም ሊበግረው አልቻለም  ። የወጣቱ ትውልድ አሻፈረኝነት ከአድማስ እስከ አድማስ  እየተቀጣጠለ እንጅ እየቀዘቀዘ በመሄድ ላይ አይታይም ። የዐለም አቅፍ ሁኔታም፤ ለወያኔዎቹ የማይመቻቸው እየሆነ መጥቷል  ። የኢትዮጵያም ጠቅላላ ሁኔታዎችና ገፅታም፤ በሀብት ብክነት፤ በታሪክ ብክለት፤ በሀገር ክስመት፤ በወጣት ዕልቂት፤ በምሁራን ፍልሰት፤  የምትታመስ  ሀገር አድርጓታል  
ሕዝቧም፤ በኢትዮጵያዊነት- ምልዑነት ሳይሆን ፤  ዜግነቱና ስብዕናው እንዲፈረጅ የተገደደው፤ በፍራክሽን ሂሳብ፤ አንድ አራተኛ  ፤ ሁለት ሦስተኛ ፤  በሚል ስሌት  ተሰልቶ፤ በዘርና በቋንቋ  ፍርስራሽ- በቅንስናሽ- አፈረጃጀት ውስጥ እንዲገባ ተደርጓል ። ተዋርዷል ። እየወረዱ መዋረድ፤ እየተዋረዱ አንገት መድፋት፤ አንገት እየደፉ ለመኖር ብቻ ሲባል ዕስትንፋስን ማቆየት፤ የዛሪይቱ ኢትዮጵያ ዜጎች ዕጣ- ፈንታ ሆኗል ።ይኽ አልበቃ ብሎ ፤ ሕዝቧ፤ የታሪክ ምርኮኛ፤ የፖለቲካ እስረኛ፤ ሆኖ ሰማይ ምድሩ እንዲደፋበት ተድርጓል ።ከሞላ- ጎደል ፤ ይኽንን አስመልክቶ ፤ የታሪክ ምሁራንም ፤ የፖለቲካ ልሂቃንም ሆኑ፤ የብሄር ፖለቲካ አንቀሳቃሾች ከኃላፊነት የሚያመልጡ አይሆኑም    ሁሉም እያንዳንዱ ይኽንን ስህተት ካላረመ፤ በታሪክና በተተኪው ትውልድ ዘንድ መወቀሱ- መገሰሱ አይቀርም ። 
ሀገሪቱ በሁለንተናዊ ችግሮች ተወጥራ  መገኘቷ፤  ዞሮዞሮ  ዎያኔን  ተጠቃሚ አድርጎታል    ለዚህም ነው፤ እያስፈራሩ ፤ መለማመጥ የሚል ፖሊሲ አውጥቶ እንደልቡ ለማታለል የሚፍጨረጨረው። የሁሉንም " ሀሞት ጠልቄ አውቄዋለሁ" ከሚል ሀቅ ደርሻለሁ ብሎም ደምድሟል ። የተለያዩ የማጭበርበሪያ ካርታዎችን  ለመበወዝ ጊዜ ያገኘ መስሎታል    በዕርግጥ ግን ጊዜው እየመሸበት የሚሄድ ዘረኛ አምባገነን ነው ።
ለኢትዮጵያ የነፃነት ወገግታ ለማምጣት ግን ብዙ ሥራ ይጠይቃል ። ምናልባት ተብሎ ተብሎ፤ ተደጋግም ፤ ተሰልሶ፤ ተወግሮ፤ ተደቁሶ፤ የተባለለት ስለሆነ፤ ወደ መስለቸቱ የተደረሰ  መሆኑ፤ ባይዘነጋም  የሀገራችን ችግር  የሚፈታው፤ የሕዝቡ ተበብሮ መንሳት መሆኑ ፤ የሚያከራክር አይሆንም ። ከዚህ ሀቅ በመነሳት - አሁንም አሁንም  የሕዝቡ በአንድ ላይ ሆ ! ብሎ መነሳት ሁል ጊዜ ሕያው ሆኖ ይቆያል ።  እኛም ወድደን አይደልም፤ ይህንን መሠረታዊ ጥያቄ ያለመስልቸት  ደጋግመን የምናነሳው። ይኽ ሕዝባዊ ጥያቄ እስካልተመለሰ ድረስ፤ ወያኔ እያስፈራራ - እያታለለም ሆነ  እየተለማመጠ፤ ያገዛዝ ሰንሰለቱን አጠናክሮ መቀጠሉን የቀጥልበታል  ።ይኽ እንዳይሆን ከተፈለገ፤  " የእናቴ ቀሚስ ጠልፎኝ ነው "  የሚባለውን  ተልካሻ ምክንያት አስወግዶ፤በህብረት ትግል ሀገሪቱን ከዘረኞች መንጋጋ  ማላቀቅ የውል -ይደር ሊባል አይገባው 
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም  ትኖራለች  !     

           


Thursday, February 16, 2017

eprp in Norway

የስብስባው ቦታ:
Antirasistisk Senter
Storgata 25
0103 Oslo, Sentrum
ቀን: February 18/2017
ሰአት:15-18