Sunday, March 12, 2017

"የቁርበቶችን ተግባር እኛ እናውቃለን" አለ ጅብ። (ከዳዊት ተመስገን ኖርዌ ኦስሎ)


"የቁርበቶችን ተግባር እኛ እናውቃለን" አለ ጅብ።
(ከዳዊት ተመስገን ርዌ ስሎ)
March 2017
እንደምናውቀው የጎሰኝነት ስሜት በሰው ላይ እያረፈ የወገንተኝነትን ስሜትን የሚፈጥርና
የሚቀሰቅስ መንፈስ ነው እግዚአብሔር ከፈጠራቸው ሰዎች ማህል ጥቂቶችን መርጬ ወገኖቼ
እንዳደርጋቸው የጎሰኝነት መንፈስ ይገፋፋኛል ስጽፍላቸው ወገኖቼ፣ የሰፈሬ ልጆች፣ መዶቼ፣ ያገሬ ልጆች፣ የወንዜ ልጆች በላቸው በላቸው እያለ የገፋፋኛል ለነዚህ ሰዎች ልዩ ፍቅር እንድሰጣቸው ከነሱም ልዩ ፍቅር እንዳገኝ የጎሰኝነት መንፈስ ተጽዕኖ ያደርግብኝ ይችላል እንደ ርስቶስ እርስ በርሳችሁ ተፋቀሩ ይለናል ችግሩ ሁሉን እኩል ማፍቀር አይቻልም ከብዙ በጥቂቱ ብንመለከት ከጌታ ልደት በፊት በሮብዓም ዘመነ መንግስት አስራ ሁለቱ ነገድ በአገዛዝ ተጣልተው ለሁለት ተከፈሉ አስሩ ነገድ በሰሜን ፍልስጤም በሰማርያ ተቀመጡ ከተማቸው ሰኬም ነች ምንም እንኳን የእስራኤል ዘሮች ሆኑም ከአሕዛብ በመዳቀላቸው ምክኒያት አይሁዶች ይንቋቸውና ይጸየፏቸው ስለነበር ሰማርያዊቷ ክርስቶስ ውሃ አጠጪኝ ብሎ በመጠየቁ ተደነቀች። የሱስ መልሶ የእግዚአብሔርን ስጦታ ውኃ አጠጭኝ ብሎ የለመነሽን ብታውቂ የሕይወትን ውኃ ይሰጥሽ ነበር አላት ክርስቶስ በተነገረለት ትንቢት በጠበቀው ተስፋ መሠረት ከእሥራኤል ወገን ከነገደ ይሁዳ ቢወለድም በትዕማር በራኬብ የአሕዛብ ዘር አለው አምላክነቱም ለነገደ ይሁዳ ሳይሆን ለሰው ዘር ሁሉ ነውና የአይሁዳውያን ወግ ጥሶ ሳምራዊቷን አነጋገረ እኛም የዘር የጎሣ፣የሃይማኖት ሳንባባል ሁሉም ኢትዮጵያዊ ተከባብሮ ሊኖር ይገባው ነበር ነገር ግን በዘመነ ወያኔየጎሠኝነት መንፈስ ለ 25 ዓመታት ስር ሰዶ  ገራችን ኢትዮጵያን እያንገዳገዳት ይኸው እዚህ ላይ ደርሰናል።

የሕዝብ  ብቱ አንድነቱ፣ የትውልድ ልበቱ ኃብረቱ መሆኑን አንዘንጋ በጎሠኝነት መንፈስ
ስሜት ተነሳሽነት ከጓደኞቼ ከአብሮ አደጎቼ ከሰፈሬ ልጆች ወዘተ ጋር የተመጠነ ፍቅር መለዋወጥ አይቀርም ፍቅር ዕውር ሰለሆነ አንዳንዴ የሚሄደው ጎሠኝነት መንፈስ እንደመራው ነው ጎሠኝነት የሚሰራው ስራ በተለያየ ደረጃ ለሚወገኑን ሰዎች የተለያየና የተመጠነ ፍቅር እንድንሰጥ ማድረግ ብቻ ሳይሆን ሎቹን የእግዚአብሔር ፍጡሮችን የእኛ እንዳናደርጋቸው በእኛ ላይ እያረፈ እነሱን እንድንላቸው ይገፋፋናል።  በእነሱ ላይም ያርፍና እኛን እነሱ እንዲሉን ያደርጋቸዋል የጎሠኝነት መንፈስ በቅዱስነቱ የፍቅር ምንጭ ሆኖ ሳለ በርኩስነቱ ደግሞ አንዱ ከሌላው የሚለይበትን ማናቸውንም ነገር ለማግኘትና ለማጋነን ታላቅ የማጉያ መነጥር ተሸክሞ በተለያየ ንጎዳጎድ ይታያል።

ትንሿን ልዩነት አጉልቶ ትልቅ አድርጎ በማሳየት ያቀርበዋል በትምህርት ታቸውም የምንሊክ የተፈሪ መኮንን የአዲስ ከተማ ወዘተ ተማሪዎች እያለ የለያያቸውን እንኳን አንድ
እንዳይሆኑ እንደገና በክፍል ይለያያቸዋል። ዓላማውም ግልጽ ነው እነሱ የምንላቸው በዝተው እነሱዎች ዓለምን እንዲያጥለቀልቁት ይፈልጋል። ክፋቱ እኛና እነሱ በማሰኘት አያበቃም በእነሱ መዘዝ በጎረቤት ሕዝብ ማህል የተፈጥሮ ጦርነት እንጂ የተፈጥሮ ሰላም የለም ክፋቱ ደግሞ ማለያየት ብቻ ሳይሆን ማጣላትም ነው ኢትዮጵያ የእነሱዎች መንደር መሆን የሚያስከትለውን ችግር ችግሩ ለደረሰባቸው ማብራራት አያስፈልገውም።  ነገር ግን በእነሱዎች  መንደር መኖር የቱን ያህል እንደሚያስጨንቅ እስቲ ልብ እንበለው።

 ኢትዮጵያ የሁላችን የእኛ መቦረቂያ ሆና ሳለ በጎሠኝነት መንፈስ በካሬ ስንዝር ሸንሽነን ተካፍለን በድርሻችን ውስጥ ተጨናንቀን መኖርን መምረጥ ምን ይባላል?የብሔሮች ወርቀ ዘቦ በሆነች ኢትዮጵያ የኅብረ ብሔርን የፖለቲካ የትግል ስልት ይዞ የተነሳው ኢሕአፓ የቱንም ያህል የብሔርተኛና የጎሳ ፖለቲከኞች መጠቀሚያና ሰለባ እንዳልሆነ ይታወቃል ባህሪይአቋምን የሚጠይቅ ጉዳይ ነው በተለይም ደግሞ አንድ ሰው መልካም ባህሪይና አመለካከት በዙሪያው ካለው ሁኔታ ጋር ተቃራኒ የሚሆንበት ዜ ለውጥን ለማምጣት አቋምን ይጠይቃል
በተለይ አሰራር "በበሰበሰበት" አካባቢ የሚሰራ አንድ ሰው የተበላሸውን አሰራር ለማረም የሚያደርገው ጥረት በብዙዎች እንዲጠላ ሊያደርገው ይችላል እውነተኝነት በተጠላበትና ውሸት በነገሰበት አካባቢ ለዕውነት መቆም መገለልን ሊያስከትልበት ይችላል ሰዎችን ማበላለጥ በሰፈነበት ማህበራዊ አሰራር ውስጥ ሁሉም ስው እኩል ነው የሚለውን እውነት መያዝ ገለልተኛ ሊያደርግ ይችላል።  ሆኖም በተለያዩ ህብረተሰቦች መካከል የተከናወኑ የታሪክ መረጃዎች እንዲያስተምሩን ፈር ቀዳጆች ላሉበት ህብረተሰብ አንድን ለውጥ ለማስተዋውቅ ከሚከፍሏቸው መስዋዕትነቶች መካከል አንዱ ይህ ነው የሚቀጥለው ትውልድ ትክክለኛ መስመር ውስጥ እንዲገባ ካስፈለገ ለዚያ ትክክለኛ መስመር ዛሬ መንገዱን ለመጥረግ መስዋዕትነትን ለመክፈል የተዘጋ  ሰው የመኖሩ ጉዳይ አስፈላጊ ነው የጎሰኝነት መንፈስ የፈጠራቸውን የእነሱዎችን መንደር አፍርሶ አንድ ትልቅ የእኛ ከተማ ለመፍጠርና በውስጡ እንደልብ ለመቦረቅ መፍትሔው ምንድነው? እነሱዎች ሁሉ መፍረስ አለባቸው ወይ የእኛ ከተማ የቱን ያህል ትልቅ መሆን አለበት የጎሰኝነት መንፈስ በሕይወት እስካለ ድረስ አንድ ዓይነት ሕዝብ መሆን ይቻላል ወይ? ቢቻልስ አስፈላጊ ነወይ?

በኢትዮጵያ የቀደሙት ነገሥታት ከግብር በቀር ሌላ ምንም ስለማይፈልጉ ግብራቸውን ካገኙ በየ አውራጃዎች አስተዳደር አይገቡም ነበር የጎሰኝነት መንፈስ ያሸልብ እንደሆነ ነው እንጂ ስለማይሞት በሟቹ ፋሺስት የወያኔ አለቃ በነበረው መለስ ዜናዊ አጋፋሪነት ስር ሰደደበት ኢትዮጵያ  ገራችን በግራም በቀኝም እኛ ና እነሱ በሚሉ ተያዘች አንድ ነን የሚለው ወገን ሳይቀር እኛ ለብቻችን ነን በማለት የሚችለው ጠፋ በትዕዛዝ ሳይሆን በማስተማር በመስበክ ሳይሆን ጥቅሙን በማስረዳት ሕዝቡን ስለጥቅም ሁሉም ይቅር ብሎ በጎሰኝነትን መንፈስ ላይ እንዲያምጽ ብናደርገውስ እኛ ብቻ የሚባለው ጽንፈኛ አመለካከትና በሌላውም በኩል ኢትዮጵያ የእነሱ ናት የሚል የገለልተኝነት ስሜት አሁንም አለ ኢትዮጵያዊነት እየተጎዳ የሚገኘው በዚህ መልክ ነው አሁን በሀገራችን ላይ እየተካሄደ ያለው ህዝባዊ አመጽም በሰሜኑ ሀገራችን ክፍል የሚካሄደ በጎንደር በኩል ይህ ትግል የአማራ፣የኦሮሞ፣ የክርስቲያን፣የእስላም አይደለም ይህ ትግል የሁሉም ኢትዮጵያዊ ትግል ነው።

ቱርኮች  ገራቸው ውስጥ የነበሩትን አርመኖቹን ልቅም አድርገው በመግደል የአንድን
ጎሳ ዘር ማጥፋትን መፍትሔ አድርገውት ነበር  ርመን ውስጥ ለአይሁዶች የታቀደውም ይኸው የመጨረሻ መፍትሔ የተባለው ዘዴ ነበረ ይኸው በ ገራችን ኢትዮጵያ ደግሞ አማራውን የማጥፋት ዘመቻ በተለያየ መልኩ እየተካሄደ ይገኛል እንደሚታወቀው በሰዉ ዘንድ ብዙ ዓይነት ይኖች አሉ የጥበበኞች ዓይን፣ መልካም ዓይን፣ ትዕቢተኛ ዓይን፣ ክፉ ዓይን፣ የሰነፍ ዓይን፣ የምትንቅ ዓይን፣ ምቀኛ ዓይን፣ ወዘተ.......,ይገኛሉ። ከተዘረዘሩት ውስጥ እርስዎ ምን ዓይነት ዐይን ይኖርዎት ይሆን? የሰውነት መብራት ዐይን ናት እኛስ ኢትዮጵያዊው የሆነውን የአማራ ሕዝብን በምን ዓይነት ዐይን ነው እያየነው ያለነው? ጠላት ወያኔ ጦር ሰብቆ ዘገር ነቅነቆ ሲመጣብኝ ምን ይታይዎታል? መቼስ አደገኛ ሞት ያለበትን የሚያውቀው ያልተገራ አንደበት ነው እንደማትሉኝ እርግጠኛ ነኝ ለሰውስ መልካም ማነው ቢሉ አገር፣ ለወገብስ መልካም ማነው ዝናር ብሎ ለተነሳው አማራው ኢትዮጵያዊ  ገሩንና አንድም ሕዝቡን ለመታደግ እስከተነሳ ድረስ በወያኔያዊ ዐይን ልናየው አይገባንም።

በኢትዮጵያዊነት ላይ ትልቅ የዘመቻ ግንባር የተከፈተው በንዑስና በክፍልፋዩ ደረጃ
"በጎሳ-ጎሰኝነት" አኳያ እንድናስብና እንድንወስን አዲስ የፖለቲካ ወንጌል ወያኔ መስበክ ከያዘበት ወዲህ መሆኑ ይታወቃል ዳግማዊ አጤ ምኒልክ የክተት አዋጅ ባስነገሩበት ጊዜ ሳያመነታ ምንም ሳያንገራግር አፈፍ ብሎ የተነሳው ወገን ቀደም ሲል እንደሚታወቀው የአማራው ሕዝብ የ ግንነት ባህሪው በነባራዊነት የደነደነ ስሜቱም ከ ገር ፍቅር ጋር በእጅጉ የላቀ በመሆኑ ነው የአማራው ማንነት ሲያስቡት ዛሬም ቢሆን ነገ እስከ መጨረሻውም ድረስ አትንኩኝ ባይነት ከኢትዮጵያዊነት ባህሪይ ሊነጠል አይችልም ብሎም ቢሆን ዘመን እየተቆጠረ ዘመን ሲተካ ይህ ኩሩነትና አገር ወዳድነት ባህሪይ ከነባራዊነቱ ፈቀቅ በማለት እንዳያውክ ወጣቱ ትውልድ ያባቶቹን  ግንነት ዘመናዊ በሆነ መልዕክ እንዲወርስ ማድረጉ አማራጭ የሌለው ተግባር ነው።

ሕብረ-ብሔራዊ በሆነ የፖለቲካ መርህ በመመራት ስንታገል ነው መርህ እንደ መልህቅ
የሚሆነው አንድ መርከበኛ ወደ ወደብ ሲደርስ መ መሪያ የሚያደርገው ነገር የመጣ ማዕበል ሁሉ መርከቢቱን ወዲህና ወዲያ ይዟት እንዳይሄድ መልህቁን መጣል እንደሆነ በማንኛውም የስራ መስክና ማህበራዊም ሆነ ፖለቲካዊ ውስጥ የተሰማራ ሰው ዘልቆ ከመግባቱ በፊት በቅድሚያ የመርህ መልህቁን ሊተክል ይገባዋል። እኛ ኢትዮጵያን የሚለውን መንፈስ በማስፋት እነሱ የሚባለውን የጎሳንና የቋንቋን ክልል በተሻገረ አመለካከት በመሰለፍ ስንታገል ብቻ ነው  ሀገራችን ኢትዮጵያን ነፃ ልናወጣ የምንችለው።


የወያኔን አምባገነን አገዛዝ በተባበረ ትግል እናስወግዳለን_