Friday, May 12, 2017

እኔ ልብላ አንተ ጦም እደር. http://www.finote.org

እኔ ልብላ አንተ ጦም እደር
የወያኔ መርህና የግንባር መፈክር ይህ ነው ። ወያኔ ይብላ፤ ይንደላቀቅ፤ ይክበር፤ ይግደል፤ ሕዝብ ግን ራብይታረዝ፤ይዋረድ፤ መብት አልባ ይሁን፤ የስየልም ሰለባ ሆኖ ይማቅቅ። ከ 25 ዓመት በላይ ወያኔን  አየነው፤ ታዘብነው፤መረመርነው ያው ፍንክች ብሎ ከዘረኛእትና ወሮበላነት አልተቀየረም፤አልቀነሰም ። ዶሮን ሲደልሏት በመጫኛ ጣሏት ዓይነት ጨ ሕዝብ፤ ሰላምን የናፈቀ ሕዝብ ወተ በሚል ሲደለልን፤ ሲያዘናጋን ቢከርምም ለወያኔ ምሱ መድሃኒቱ አመጽና የብረት ትግልም መሆኑን ከተረዳን ያን ያህል ዓመታት አልፈዋል ። ያልተገላበጠ ያራልንም አስተማሪ የሚያስፈልገን አልነበረም።
ከቀውስና ኢፍትሃዊ ሁኔታ ለመውጣት ዕርቅና ሰላምን ጠርተን ያገኘው የንቀትና የዕብሪት ምላሽና ወግዱ እንጂ ኑ እንወያይ እንደማመጥ አልነበረም ። ጦርነት እንሰረባችኋለን፤ ወኔ ካላችሁ ሞክሩን መንገዱን ጨርቅ ያድርግላችሁ ብለው ተሳልቀውብን ነበር ።  በቀጥታም ስንቱን ሴጋ ገድለውና አስረው አሰቃይተው በገቢር ትምህርት ሰጥተውናል አሳይተውናል። ምንም የተቀየረ የለም ።የመለስና ስብሓት ዘረና ቡድን ኢትዮጵያን ጠልቶ ሊያወድማት የተነሳ ነበርና ከዚህ ምንም ፈቀቅ ለቀቅ ሳያደርግ ይኸው ለዓመታት በላያችን ላይ ሰፍሯል ። ታዲያ ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማን ምን አመጣው? ክእባብ እንቁላል ርግብ ሊፈለፈል ጥበቃው እስከመቼ? ወያኔ ጭንቅ ሲያጋጥመው፤ ሲወጠርና ብርክ ሲመጣበት--በመሰረቱ የወያኔ መሪች ፈሪዎች ናቸውና--ማደናገሪያና ጊዜ መግዣ መንገዶች አሉት ። ሰላም ፈላጊ ይመስላል፤ ድርድር እባካችሁን ጩኸት ያሰማል፤ አጀንዳ ያስቀይራል  ወዘተ በ1997 ዓ.ም. በግልጽ አይተነዋል ።ዛም የሕዝብ አመጽ ሲወጥረው ያንኑ ሊደግም እየጣረ ነው ። ከሶስት ሺ ያላነሰ ዜጋን ገድሎ፤ከ 40 ሺ በላይ አግቶና ደብድቦ እንወያይ የሚለውን ሸንካላ ጥሪ ሲወረውር እንዴታ ብለው የተነጠፉለት መኖራቸውንም መታዘብ ችለናል ። ይጠራናል ብለውም በተለይ በባዕድ ሀገር ያሉ ተልካሻ ቡድኖችም ዝግጁ ነን፤ እንዲህ እንዲያ ይደረግ  እያሉ ሲቋምጡ ታዝበናል ። ወያኔ ግን ዘሬን ብተው ይዘርዝረኝ ነውና በአብዛኛው ከራሱ ፍጡሮችና ተለጣፊዎች ጋር የይስሙ ውይይት ጀምሮ ሌሎች ደግሞ ትንሽ ጠጠር ሲሉበት ወደ ማቆሙ ገፍቶ ተለያይቷቸዋል ። 
ወያኔ ስግብግብ ጸረ ኢትዮጵያ ሀይል መሆኑንና ካልተወገደም ሀገራችን እንደምትጎዳ በተግባር አሳይቶናል ። ኮሶ ግቶ!! ውይይት ሲል ዋናው መፍትሄው ወይም መንገዱ ያ ሆኖ አይደለም ። ዋናው ዛሬም እንደ ትላንት በሀይል መጠቀም ነው ። ከጥቅምት ጀምሮ የፈሠሰው ደም ይህን ያመለክታል ። በአዋሽ በረህ ስየል እየተቀበሉ ያሉት ይህን ይመስክራሉ ። ወያኔ ለረጅም ጊዜ የገዛው ሕዝብን ከፋፍሎ በማዳከሙና የጋራ ትግልን በማስወገዱ ስለሆነ አሁንም የወያኔ ዋናው መሳሪያ ሕዝብን መከፋፈል ነው ። በመሆኑም ቅጥረኞቹን በሰፊው በሀገር ቤትና በውጭም አሰማርቷል ። ጽንፈኛና ብሄርተኛ አቅዋም የያዙ መስለው፤ ለሕዝብ ተቆርቋሪ መስለው ሕዝብን ግን ባለፈ ታሪክ እያናቆሩ፤ በጸረ ወያኔ ሀገር ወዳድ ድርጅቶች ላይ በጸያፉ እየዘመቱ ለወያኔ ከፍተና ጠቀሜታ እንዲሰጡ አሰማርቷቸው ይኸው ደፋ ቀና ሲሉና ሲያጓሩም ይደመጣሉ ። ይህ ነው የወያኔ መንገድ--ሕዝብን እርስ በርስ ማናቆር፤ ሀገር ወዳድ ድርጅቶችን ማዳከም፤ ከፋፍለህ ግዛ፤ በክስና አሉባልታ መሪዎችን ማጥፋትና ሲመቸውም መግደል ማፈን  ።  ወያኔ ከዚህ ከራቀ ተዓምር ቢባል ይገባዋል ። ኢትዮጵያ ደግሞ ተዓምር ማየት ተሳናት ሀገር ከሆነች ዘመናት አልፈዋል ።

አሮጌ መጥረጊያ ቤት አያጠራም ተብሏል ። ለወያኔ ተንኮል ነጋ ጠባ  ሰለባ መሆንም የትም የሚያደርሰን አይሆንም ---ከጉዳት በስተቀር ። የከፋፋይ ቅስቀሳን ስንሰማም ቆይተናል--ለዚህ ጆሮአችንን መዝጋቱ መድፈኑ ተገቢ ነው ። ትላንት ቆሻሻ ያልነውን ዛሬም ለመሸከም ዝግጁ መሆን አይጠበቅብንም ።የገማ የገለማ ስርዓትን ይዘት ለመድገም መጣሩ ለውጥን ማምጣት አይደለም ። የነገ ኢትዮጵያ ከአድህሮትና ዘረኛ ስርዓቶች በመሰረቱ የተለየች መሆኗ የግድ ነው ። ከጥበትም ከትምህክትም የራቀች የጸዳች ። የዛሬይቱን ኢትዮጵያ ድሪቶ ደራርቶ አዲስ የክብር ካባ ለማስመሰል የሚደረገው ጥረት ሁል ውድቅ መሆን ያለበትና የሚወድቅም ነው ።
ፍትህ ዴሞክራሲ ለኢትዮጵያ !
ወያኔ በጋራ ትግላችን ይውደም !!