Wednesday, June 7, 2017

የወያኔ እብደት ቢንያም ሙሉጌታ

የኢትዮጵያ ህዝብ ላለፉት 26 ዓመታት የወያኔ የግፍ በትር ቢያርፍበትም የሚፈራና የሚሸማቀቅ ህዝብ አለመሆኑን አስመስክሯል:: ወያኔ ዜጋውን ከመሬቱ እያፈናቀለ ቆሻሻ ውስጥ እንዲኖር፣ ቆሻሻ እንዲበላ ብሎም የቆሻሻ ናዳ ተንዶበት እንዲሞት በማድረግ የበለጠ ጭካኔውን አሳይቷል:: ኢትዮጵያ ሀገራችንን የአይምሮ መታወክ ችግር ያለባቸው ስብስቦች እንደሚመሯት የታየበት አጋጣሚ ነው :: በሰው ደም በሚሰሩት ግፍ ብዛት የአይምሮ መታወክ ውስጥ እንደገቡ ድርጊታችው ይመስክራል::
በቆሼ በሚኖሩ ወገኖቻችን ላይ የደረሰው አደጋ የሚያሳየው ይህንኑ ነው ::የእብደት ትልቁ መመዘኛ የአእምሮ ቀውስ ያለበት ሰው ቀውስ ውስጥ እንዳለ አለማመኑ ነው :: ታዲያ እነዚህ ያልተማሩና ደናቁርቶች የወያኔ ባለስልጣናት ሀገራችን ኢትዮጵያ በተለያየ መልኩ ችግር ውስጥ እንድትገባ ምክንያት ሆነዋል ::
የወያኔ ባለስልጣናት እጅግ የበዛ ቀጣፊነታቸው ጨካኝነታቸው ኢትዮጵያውያኑ ላይ እንዲህ ያለ ውርደት አስከትሏል :: በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ በሀገራችንና በዜጎቻችን ላይ ብሄራዊ ውርደቶች በተደጋጋሚ ሲፈጸምብንና ሆን ብለው ሲያስፈጽሙ አይተናል ::
በጋምቤላ ክልል ህጻናት እንደ ዕቃ ሲዘረፉ፣ በደብረዘይት በኢሬቻ በዓል ላይ ዜጎች በጥይት ሲጨፈጨፉ በየመን ፣ በደቡብ አፍሪካ ዜጎች ሲገደሉ፣ በጎማ ሲቃጠሉ፣እንዲሁም በማእከላዊ እስር ቤቶች የሚሰቃዩ ዜጎችን ጨምሮ አሁን በቆሼ የደረሰውን
አደጋ ስንመለከት በወያኔ መንግስት በአጭር ጊዜ ውስጥ ይህ ነው የማይባል ብሄራዊ ውርደቶች እንደተፈራረቁብን ልብ እንላለን::
ወያኔዎች እብደትንና እድገትን አለዩም እብደታችውን እድገት እያሉ ያወራሉ:: አንድ ሀገር አደገ የሚባለው ህዝቡ በቂ መኖሪያ ሲኖረው የነፍስ ወከፍ ገቢ የዋጋ ግሽበትን ሲያሸንፈው በችግር ምክንያት ሰዎች መሰደድና መራብ ሲያቆሙ ተመጣጣኝ ገቢ ከተመጣጣኝ ወጪ ጋር ሲሰተካከል እንጂ: አንድ ስው በቀን 100 ብር እያገኘ በቀን 400 ብር የሚያስወጣ ኑሮ ሲኖር አገር አደገ ሊያስብል አይቻልም ::
ወያኔ እድገት እያለ የሚቀጥፈው ቅጥፈት ለሚድያ ፍጆታ እንጂ እውነትነት የሌለው መሆኑ ማንም የሚረዳው ነው ::ለዜጎች ህልውና የሚሰጥ መንግስት ባለመኖሩ ዜጎች በድህነት ቀንበር ውስጥ ይማቅቃሉ::ህዝባችን ወያኔ በቃን ስልጣን ለህዝብ ያስረክብ ሲል አምባገነኑ ወያኔ ግን ጥልቅ ተሃድሶ ላይ ነን በማለት መቀደድን ተያይዞታል::
የእነሱ ጥልቅ ተሃድሶ ለህዝብ ምንም ለውጥ እደማያመጣ እያየነው ነው ::ስርዓቱ ህዝቡን መምራት ማስተዳደር አቅቶታል
ህዝብም በቃኝ እያለ ነው:: ጨቋኝ አገዛዙ የህዝብ ጠላት የሆነ ገዥ አደገኛ ዘረኛነቱን በማራመድ ኢትዮጵያውያንን በገዛ ሀገራችን የበይ ተመልካች ያደረገ የአንድ ዘር የበላይነትን ለማረጋገጥ ዛሬም የማይደራደር በዘረኛነት በሽታ የተጠቃ ያልሰለጠነ አይዲዮሎጂ አራማጅ ስርዓት ነው::
በወያኔ ስርዓት አስነዋሪውና ስር የሰደደው ዘረኛነት ነው::ሰውን በተወለደበት አካባቢ በሚናገረው ቋንቋ በዕምነትና በባህል ማግለል በነገራችን ላይ ወያኔ ይህንን የዘረኝነት ልክፍት ተቃዋሚ ወደሚባሉት በዘርና በአካባቢ ለተሰባስቡት ቡድኖች ጭምር የኢትዮጵያዊነትን አስተሳሰብ ካባ እንዲያወልቁ በማድረግ እርሱ በሚፈልገው መንገድ እንድጓዙ ምክንያት ሆኗል ::
አውሮፓ እና አሜሪካ እየኖረ እንኳ የአማራ፣ የኦሮሞ ወ..ተ እያሉ በአካባቢያቸውና በመንደራቸው ተወስነው የቀሩ ወደ ኋላ የሚያስቡ የነሱ ዘር የተባረከ እንደሆነ ብቻ ማሰብ የሚፈልጉ የወያኔን የ26 አመት ህልሙን እውን ያደረጉለት እነዚህ የመንደር የጎጥ ስብስቦች ናቸው:: በሀገራች ኢትዮጵያ ያለውን የፖለቲካ ችግር ይባስ እያባባሱ ይገኛሉ ::

በቅርብ ወራቶች ውስጥ በሀገራችን ኢትዮጵያ የተፈጠሩት ተቃውሞ እንኳን ስንመለከት ዘርንና አካባቢን ተገን ያደረገ አልነበረም ::በጎንደር የነበረው ተቃውሞ ተደጋግሞ እንደተነገረው ከራሱ ከኢትዮጵያዊው ጎንደሬ እንደተሰማው በኦሮሚያ የነበረውም ተቃውሞ ከራሱ ኢትዮጵያዊ ኦሮሞ እንደተሰማው የተናጠል ግድያ እስራትና ስቃይ እንዲቆም ስርዓቱም እንዲያበቃለት የጠየቀ ነበር ::
ዛሬ ግን በዘር የተደራጁና ለግል ስማቸው የሚሮጡት ገንዘብና ንዋይ ፍለጋ ለውጥ ፈላጊውን ኢትዮጵያዊ ዜጋ በውሽት ፖለቲካ ግራ እያጋቡትና እየበዘበዙት ይገኛሉ::ስራዎቻቸው ሁሉ ለመገናኛ ብዙሃን የሚውል የይስሙላ ነው::ታዲያ እነዚህ በዘር የተደራጁ ዛሬ ላይ ከወያኔ በማይተናነስ መልኩ ሀገሩን ለሚወደው ኢትዮጵያዊ ዜጋ ከፍተኛ ስጋት ሆነዋል::
አንድ አመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ የአንድ ዘር ስም በመጠቀም ብቻ በትውውቅ የተሰባሰቡ ሰዎች ከሰባት የሚበልጡ ድርጅቶችን አቋቋምን ሲሉ ከማስደንገጥ ባለፈ ግርምት ውስጥ ከቶናል የወያኔ መልእክተኞች መሆናቸው በእርግጠኝነት መናገር ይቻላል::
በኢትዮጵያ አንድነት በማይደራደረው ኢሕአፓ ላይ ጣታቸውን ሲጠቆም የኢሕአፓ ህብረ ብሄራዊ አደረጃጀት እንቅልፍ ሲነሳቸው ባገኙት አጋጣሚ ውሸቶችን በመደርደር ለመክሰስስ ሲሞክሩ አይተናል:: ምን ያለበት ምን አይችልም ነውና ነገሩ ዋናው የኢትዮጵያ ጠላት ወያኔን ትተው ጊዜያቸውን በሙሉ የወያኔን እድሜ ለማራዘም ጠንካራ ድርጅት እንደሆነ በሚያውቁት ኢሕአፓ ላይ ያጠፋሉ ::ወያኔንና በዘር በአካባቢያቸው ተደራጅተው ኢትዮጵያን ለማጥፋት የሚሯሯጡትን ልንታገላቸው ይገባል::
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !!! 

No comments:

Post a Comment