Tuesday, March 27, 2018

የወያኔ ፀረ-ኢትዮጵያዊነት ገሀድ ወጣ፤ ለጋራ ጥያቄ የጋራ ትግል ያስፈልጋል።


የወያኔ ፀ-ኢትዮጵያዊነት ገሀድ ወጣ፤ ለጋራ ጥያቄ የጋራ ትግል ያስፈልጋል።
መጋቢት14 ቀን 2010ዓ.ም
page1image3965569840 page1image3965570240
የወያኔ ዘረኛ፣ መድልኦዊ የአምባገነን አገዛዝ ኢትዮጵያ አገራችንን የባሕር በር አልባ ያደረገ፣ መሬታችንን ለሱዳን አሳልፎ የሰጣ፣ አንዲሁም የአገሪቱን ለም መሬቶች ለባዕዳን ፣ ለአራብ፣ለሕንድ፤ ለቱርክ፣ ለማሌዢያ፣ --- ወ.ዘ.ተ ለብዙ ዓመታት ከመቸብቸብ አልፎ ገንዘቡን የበላ፣ የአገሪቱ የስልጣኔ ምንጭና እድገት መሰረት የሆነውን ትምህርት ለመግዳል ባለው መሠሪ ዓላማ ትውልድ ገዳይ የትምህርት ፖሊሲ በባለሙያዎች ሳይሆን በካድሬዎቹ አማካይነት አንዲቀረጽ በማድረግ ትምህርት ላይ ትልቅ ወንጀል የፈጸመ፣ የአገሪቱን ታሪክ ለማጥፋት ባለው ቁርጠኛ አቋሙ በዩኒቨርሲቲዎች፣ በኮሌጆች፣ በሀለተኛ ፣ በመለስተኛና በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የታሪክ ትምህርት እንዳይሰጥ ወይም የውሸት ታሪክ ትምህርት እንዲሰጥ ያደረገና በሕዝቡ ዘንድ ተወዳጅ ከሆኑት ከድርጅት መሪዎች እስክ ግለሰብ ድረስ የገደለና ያስገደለ የማፊያ ቡድን ነው። በነዚህ ታላላቅ አገራዊ ወንጀሎችና ክህደት ነው ወያኔ ጸረ-ኢትዮጵያ፣ ጸረ-ኢትዮጵያዊነትና ጸረ-ሕዝብ ነው የተባለው። ይህን የክህደት ተፈጥሮአዊ ተግባሩን ወያኔ ከስልጣን በሕዝብ ትግል እስከሚወገድ ድረስ ይቀጥላል እንጂ ይተዋል ብሎ መጠበቅ የዋህነት ነው።
ወያኔና ተባበሪ ተላጣፊ ድርጅቶች በስብሰናል የኢትዮጵያ ሕዝብን ይቅርታ እንጠይቃለን ያሉቡት ቃል ውሎ ሳያድር መሰሪው ወያኔ የአስቸኳይ ጊዚያዊ አዋጅ በማወጅ ቅዳሜ መጋቢት 1 ቀን 2010 ዓም በደቡቡ የአገራችን ክፍል በቦረና ዞን በሞያሌ ከተማ የወያኔ አጋአዚ ነፍሰ ገዳይ ጦር ቤት ለቤት በማሳስ፣ በመንገድ ላይ ሰላማዊ እንቅስቃሴ በሚያካሄዱ ዜጎቻችን፣ በቡና ቤት፣ በሻይ ቤቶች ፣ በገበያና በሱቅ ሆነው መደበኛ ስራቸውን ሲያከናውኑ በነበሩ የ7 እና የ10ዓመት ህፃነትን ጨምሮ ከ13 በላይ ዜጎችን አልሞ በመተኮስ በግፍ ሕይወታቸውን አጥፍቷል። በርካቶችንም አቁስሏል።
በዚህ የግፍ ግድያ ወቅት የሙያ አጋራችን የሆነው በ2008 ዓም በኦሮሚያ ክልል በትምህርት ቤቱ ውስጥ ላበረከተው ትልቅ የትምህርት ስራና ላሳያው የሙያ ስነምግባር ሁለተኛ ደረጃ ተሸላሚ ፣ በአካባቢው ሕዝብ፣ በትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ ተወዳጅ ፣ የአንድ ልጅ አባት ፣ የ34 ዓመት ጎልማሳ ርዕሳ መምህር የነበረው/የሆነው ታምሩ ነጌሶ በእረፍት ቀኑ ቅዳሜ መጋቢት 1 ቀን 2010 ዓም ጊዜውን ሰውቶ በመዶ ሚጎ ት/ቤት ውስጥ ከተወሰኑ መምህራን ነገር ያደርገው የነበረውን የትምህርት ስራ ጨርሶ ወደ ቤቱ ሲመለስ መንገድ በማቋረጥ እያለ የአግኣዚ ነፍሰ ገዳይ ጦር በሶስት ጥይት ደብድቦ ሕይወቱ እንዲጠፋ አድርጓል።
ይህን የወያኔን የግፍ ግድያና የጅምላ ጭፍጨፋ በመሸሽ ከ60ሺ በላይ ኢትዮጵያውያን ወደ ጎረቤት አገር ኬኒያ ሊሰደዱ በቅተዋል።የወያኔን ዘረኛ ድርጊት የሞያሌ ከተማ ካንቲባ ለመገናኛ ብዙኃን እንደገለጹት ሠራዊቱ የባእድ ጦር እንጂ የኢትዮጵያ አይመስልም ብለዋል። ታዲያ በዚህ ድርጊቱ ወያኔ ኢትዮጵያዊ ነው? ለኢትዮጵያ ሕዝብ የቆመ ነው? ቀደም ሲልም በተለያዩ ቦታዎች ይኖሩ የነበሩ ኢትዮጵያዉያንን ከትውልድ ቄያቸው ክኖሩበት ስፍራ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን እንዲፈናቀሉ ያደረገ ፀረ-ሕዝብ ዘረኛ ቡድን ነው። ላለፉት 27 ዓመታት ወያኔ ኢትዮጵያዊ አይደለም የተባለው እነሆ ዛሬ ገሀድ ወጣ። ሰላማዊ ሕዝብ በወያኔ ሠራዊት በጠራራ ጸሐይ በጥይት እየተደበደበ ይገኛል። በስደት የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር አባላት አስተባባሪ ኮሚቴ ይህን የወያኔን በቦረና በሞያሌ ከተማ ህዝብ ላይ የፈጸመውን አራማኔያዊ ግድያ፣ በሕዝብ ላይ ያደረሰውን የአካል ማቁሰልና ጉዳት፣ ማፈናቀልን በጥብቅ ያወግዛል፤ ይኮንናል። እንዲሁም በሌሎች ቦታዎች በጎንዳር፣ በወልቂጤ፣ በነቀምት፣ በደምቢዶሎ ---ወ.ዘተ በሚገኙ ኢትዮጵያዉያን ወገኖቻችን ላይ የፈጸመውን ግድያ፣ አስራት፣ የመሬት ቅሚያ፣ የትምህርት ክፍለ ጊዜያት ብክነትን፣የተማሪዎችና የመምህራን እስርን፣ የአካዳሚክ ነፃነት መታጣትን በጥብቅ ይቃወማል። 
በአሁኑ ሰዓት የወያኔ አገዛዝ ከምንጊዜውም በላይ በፖለቲካ ፣ በኢኮኖሚና በማህበራዊ ቀውሶች ውስጥ ተዘፍቆ ይገኛል። የሕዝቡ በወያኔ አልገዛም፣ እምቢ አሻፈረኝ በማለት የጀመረውን ሕዝባዊ ሰላማዊ ትግል፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ፣ ከቀን ወደ ቀን እያደገ የመጣበት፣በወያኔና በኢትዮጵያ ሕዝብ መካከል ያለው ቅራኔ ከመክረሩ የተነሳ ሊበጠስ የተቃረበበት ጊዜ ላይ እንገኛለን።
በሌላ በኩል ደግሞ የወያኔ አገዛዝ እንደቀድሞው ሊገዛ ያልቻለበት በሁሉም መስክ በኢትዮጵያውያን ዘንድ ተቀባይነትን ያጣበትና እየተዳከመ የመጣበት ሁኔታ ይስተዋላል። እኩል ባልሆኑ ኃይሎች መካከል የእኩልነት ሁኔታ የተፈጠረበት ክስተት ነው( Equilibrium between unequal forces)። ለስርዓት ለውጥ ነባራዊ ሁኔታዎች የተሟሉበት ነገ ግን ይህን የሕዝቡን ትግል ከዳር ለማድረስ ህሊናዊ ሁኔታዎች ያልተሟሉበት በሂዳትም ክፍተቱን ለመሙላት ትግል እየተካሄደ ያለበት ሁኔታ ላይ ደርሰናል።
የሕዝቡ ጥያቄ ከአካባቢ የውስጥ ጥያቄዎች በመዝለል አገራዊ ቅርዕ እየያዘ የመጣበት ሁኔታ ይታያል።ወያኔ በቃ፣( Down Down Woyane) ወያኔ ይወደም ፣በወያኔ አንገዛም ፣ ሁሉንም ያካተተ የሽግግር መንግስት ይቋቋም ፣ የአዋጅ ጋጋተ የሕዝቡን ትግል አይገታም፣ ስር ነቀል ለውጥ ይደረግ ወያኔ ይወገድ የሚሉ ሕዝባዊ መፈክሮች በስፋት እየተስተጋቡ ይገኛሉ። የቀረው ይህን ወሳኝና ወቅታዊ መፈክሮችን በማንገብ በየአቅጣጫው በሁሉም ስፍራ እየተፋፋመ ያለውን የሕዝቡን እምቢተኝነት የአልገዛም ባይነት እርምጃዎችን ከግብ ለማድረስ ትግሉን ማስተባበርና ማስተሳሰር ነው። ለጋራ ጥያቄ የጋራ ትግል ያስፈልጋል። ስለዚህ በተለያዩ ቦታዎች በተለያዩ ስሞች በግንበር ቀደምተኝነት ትግሉን የሚካያሄዱ ወጣቶች በጋራ-በህብረት እንዲነሱ ማድረግና መርዳት የጊዜው ጥያቄ ነው። አገራችን ኢትዮጵያ የሁላችንም ናት ከወጣቶቹ ጎን ሁላችንም መቆም አለብን። ለወጣቶቹ የቅርብ አጋዥ ኃይል መምህራን ናቸው። መምህራን በ1966ቱ አብዮት ወቅት ከወጣቶች ጎን በመቆም ለለውጡ መወለድ አስተዋጽኦ እንዳደረጉ ሁሉ ዛሬም የትግል ልምዳቸውን በመጠቀም በሰሜን በደቡብ፣ በምስራቅ በምዕራብ እንዲሁም በመሐል አገር እየተቀጣጠለ በወጣቱ ግንባር ቀደምተኝነት የሚካሄደውን ትግል አገር አቀፍ ቅርዕ እንዲይዝ ማስተባበርና ማያያዝ ታሪካዊ ግዴታቸው ነው።መምህራን በሁሉም ቦታ የስራ ማቆም አድማ በማድረግ ትግሉ ይበልጥ ጉልበት እንዲያገኝ የድርሻቸውን እንዲወጡ በስደት የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር አባላት አስተባባሪ ኮሚቴ በዚህ ወሳኝ የትግል ወቅት ጥሪውን ያቀርባል።
ሕዝባዊ አመጹ ተፋፍሞ ይቀጥል!!!
የወያኔ ነፍሰ ገዳይ አጋአዚ ጦር ለፍርድ መቅረቡ የማይቀር ነው!!! ለጋራ ጥያቄዎችንን መልስ ለማግኘት የጋራ ትግል ይስፈልጋል!!! 

Sunday, February 4, 2018

ትግላችን መራራ ቢሆንም፣ግብአችን ዕሩቅ አይሆንም!!(ዳዊት ተመስገን,ከኖርዌ )

04 February 2018
እንናገራለን እንጂ አንማታም የ ገር ፍቅር ከሰዎች ፍቅርና ከሰው ሰውኛ ጉዳዮች ይነጥላል እንዴ?የህወሓት አካል የሆኑት የኦህዴድና የብአዴን ሞግዚቶች ስለ ኢትዮጵያ አንድነት ስብከት የ መሩት ትንሽ ሰነባብቷል።ሰውየውከአነጋገሩ ክትነትና ከሚሰጠው ጣዕመ ምስጢር የተነሳ ሲሰሙትና ሲያዳምጡት ቢውሉ ቢያድሩ አይሰለችም
ምክኒያቱም የኢትዮጵያ አንድነት ሲጠራ ደስ ይላል።ነገር ግን ኢትዮጵያን በመጥራት ብቻ ያለ ትግበራ ይሆናል እንዴ?እኔን ግራ የገባኝ ከ27 ዓመት በኃላ የኢትዮጵያ አንድነት የሚለው አባባል ያውም በባህር ዳር ስብሰባ ላይ
ለአማራው ሕዝብ ኢትዮጵያዊነት ሲሰብኩ ለቀባሪው አረዱት አይሆንም ብዬ ነው።
ሐሰትና ስንቅ እያደር ይቀላል እንዳይሆን እሰጋለሁ ወይም ደግሞ ከእሪያ በግ እንደማይወለድ ሁሉ ከሐሰተኛም ሕልምም ቁም ነገር አይገኝም እንዳይሆን።
ጦርነታችሁ ስጋና ደም ሆነው ከሚታዩ ጋር ሳይሆን ከጨለማ ገዢዎች እንጂ እንዳለው የጨለማ ገዢ
ከሆነው ከድንቁርና ከውሸት ጋር ከተላበሰው ከህወሓት ግብግብ ገጥሞ ሲያሸንፉ እኛ ያኔ የዓይን ምስክር መሆን
እንችላለን።የህወሓት የጋሻ ጃግሬ ሆነው እንዲህ ቢሉን ያስገደዳቸው የሕዝብ ሐብቱ አንድነቱ፣የትውልድ ጉልበቱ
ኀብረቱ ስለሆነ ብቻ ነው።በሌላ አነጋገር ህወሓት ሕዝባዊ አመፅ ስለተገደደ እንጂ ምነዋ የአኖሌ ሃውልት ጡት
የተሰራበት ቦታ ሄደው ወይም አንቦ፣ወለጋ፣ትግራይ ላይ ነው የኢትዮጵያ አንድነት መስበክ ያለባቸው ምከኒያቱ
ኢትዮጵያዊነት የተናነቃቸው እዚህ ክልል ላይ እንጂ ኢትዮጵያዊነት ለአማራው አይሰበክም የምለው።
በእኔ በኩል አመንዝራ ካሏት ብትቆርብም አያምኖት ነው በጣም የሚገርመው ኦህዴድና ብአዴን የሚባሉ
የህወሓት ደቀ መዝሙሮች የጎጃምን ሕዝብ በኢትዮጵያዊነት ካላጠመኳችሁ በማለታቸው ምነው ከረፈደ ለማለት
ነው።መቼስ ድሮ በአባቶቻችን ጊዜ እንዲህ ይባል ነበር ባሪያ ሦስቱን ነገሮች ካላወቀ ታዝዞ መኖርን አይችልም
ዕረፍትንም አያገኝም።እነሱም የሚመራውና የሚቃኘው፣ታማኝነት እንደ ቸር ጠባቂ ሆኖ የሚጠብቀው ተግሣጽ
ከመጥፎ ልማድ የሚመልሰው ፍርሃት ናቸው።ባሪያ እየተሰደበ ቢገዛ ይበረታል፣እየተሳደበ ቢገዛ ግን አይበረታም።
ይህ አባባል አሁን አይሰራም እነዚህ የህወሓት ሞግዚቶች ኦህዴድም ሆነ ብአዴን የኦሮሞና የአማራውን ሕዝብ
አይወክሉም።የኢትዮጵያን ትግል ለማኮላሽት በአገዛዙ ከሚጎዱ ሰዎች ይልቅ በአገዛዙ ምክኒያት የሚጠቀሙ ይባዛሉ
ልበል የኢትዮጵያን ሕዝብ ትግል አቅጣጫ ለማሳትና ብሎም ጠላት ወያኔ ትንፋሽ እንዲወስድ የተደረገ አባባል ነው
የምለው።አዳዲስ የትግል ስልቶችን በመ መር ወጣቱ ንቃታቸውና ብቃታቸውን በማቀናበር እንዲሁም በማቀላጠፍ
በተለያየ ስልት ጉድ የሚባልላቸውን ሰዎች በታትኖ ምንም ትግሉ አቅም እንሌለው ሰው እንዲኖሩ የሚያደርግ አንድ
አስቸጋሪና እጅግ የተለመደ ችግር ቢኖር የትኩረት ችግር ነው።እንደምናውቀው እስከ አፍንጫው ድረስ ዘመናዊ
መሣሪያ ታጥቆ የመጣው ጠላት ፋሺስት ኢጣልያ ወራሪ አፈር ግጦ ድል የተመታበትን የዓድዋ ዘመቻን ዘወር ብለን
ብናስተውል የኢትዮጵያ ሕዝብ አንድ አካል አንድ አምሳል ሆነው ጠላትን ድል ማድረጋቸው እንገነዘባለን።ምነው
ቢሉ እምየ ምንሊክ የክተት አዋጅ ባስነገሩበት ጊዜ ሳያመነታ አፈፍ ብሎ የተነሳው ወገን ቀደም ሲል በተለያዩ
ጹሁፎቼ ገልጨዋለሁ።የ ግንነት ባሕርይው በነባራዊነት የደነደነ ስሜቱም ከፍቅረ  ገር ጋር በእጅጉ የላቀ በመሆኑ
ነው።ኢትዮጵያዊ ስሜት ይህ መሆኑ እየታወቀና የገድል ባለቤታቸውንም የማይታበል ሆኖ ሳለ አንዳንድ ጉዳይ
ተሰምቶ እንደማይታወቅ እንግዳ ሊሆንብን አይገባም።በእኛ በአሁኑ ጊዜ የሚያሳዝነው በአጭሩ የወደፊት
ተመልካችነት ሊኖረን አልቻለም።
ስለዚህ ዘወትር ከራሳችን ይልቅ ወደኃላ ተመልካችና አወዳሽ ነን እዚህ ላይ ልትገነዘቡልኝ የምፈልገው ለትግሉ
መስዋዕት የሆኑትን ወይም ኢትዮጵያ  ገራችንን ላቆዮልን አባቶቻችንን ለማለት ፈልጌ አይደለም የወደፊቱን በጉጉት
የምንመለከት የወደፊቱ ብርሃን እንዳይጠፋ የምንባዝን የምንደክም አይደለንም።በትክክል በኢትዮጵያ ሕዝብ
ሳይመረጡ ነገር ግን ህወሓት በሞግዚትነት የሰየማቸው የኢትዮጵያ አንድነት በማለታቸው በጣም ደስ ያሰኛል።
እውን ጥላቻን አስወግዶ ከሞግዚትነት ወደ ኢትዮጵያዊነት መጣን ሲሉ እነዚህ ወንበዴዎች ደስ የሚያሰኝ ቢሆንም
ነገር ግን በግማሽ እውነታን ይዞ ኢትዮጵያዊ ነኝ ማለት አይቻልም።ህወሓት በበኩሉ ሁሉም በየዘሩ ከረጢት
እየተፈላለገ እንዲቋጠር ያልማሰው ስር ያልነቀለው ድንጋይ የለም።ከህወሓት ጋር ተቀናጅቶ የሚኖር በየወቅቱ
እየተበረዘና እየተንጋደዱ ቃላትና ንዑስ ሐረጎችን እውነተኛ ትርጉም በማስመሰል የሚንቀሳቀሱትን በሚገባ መረዳት
ያለብን ይመስለኛል።በኢትዮጵያዊው ዜጋ ደምና አጥንት የተገነባውን አንድነትና ተዋሕዶ የተዛመደውን ነጥሎ
ለማውጣት የማይቻለውን የተፈጥሮ  ግንነት ለማደስና ስርዓት ለማስያዝ የተሠራ መሆኑን ለመገመት አያዳግትም።
እንዳለመታደል ሆኖ ነው እንጂ በእርግጥም ሲያስቡትም ዛሬም ቢሆን ነገ እስከ መጭረሻውም ድረስ አትንኩኝ
ባይነት ከኢትዮጵያዊነት ባሕርይ ሊነጠል አይችልም።ብሎም ቢሆን ዘመን እየተቆጠረ ዘመን ሲተካ ይህ ኩሩነትና
 ገር ወዳድነት ባሕርይ ከነባራዊነቱ ፈቀቅ በማለት እንዳያውክ አሁንም ወጣቱ ትውልድ ያባቶቹን  ግንነት
እንዲወርስ ማድረጉ አማራጭ የሌለው ተግባር ነው።በኢትዮጵያ ውስጥ በግፍ በጥይት ተደብድበው የወደቁ
ብዙዎች ናቸው፣ነገር ግን በነገረ ሠሪ አንደበት እንደጠፉት ባይሆንም ቅኑ።
ሰዎች ከሚወቅሳቸው ዳኞች ይልቅ የገዛ ህሊናቸው እየወቀሰ የሚያሰቃያቸው እጅግ ብዙ ቢኖሩም።የእውነተኛ
ተግባር ምንጩ ኢትዮጵያዊ ማንነት ነው ስለዚህም የምናደርጋቸው ነገሮች እንደየ ሰው ሁኔታ የሚለዋወጡ ከሆነ
እነዚህ የምናደርጋቸው ነገሮች ከእውነተኛነት የመነጩ ሳይሆኑ ከጥቅም ከፍርሃት ወይም ከተለያየ የራስ ወዳድነት
አመለካከቶች የመነጩ እንደሆኑ ጠቋሚ ነው።አክባሪ ኢትዮጵያዊ ማንነት ያለው ሰው የዘርን የሃብትን የዕውቀትንና
የመሳሰሉትን ሁኔታዎች ሳያይ ሁሉንም እኩል ያከብራል።እንቅስቃሴ የሌለው የሌሊት ህልም ቅዠት ነው።እርምጃ
የማይወሰድበት የቀን ህልም ደግሞ ድንዛዜ ነው።እውነቱ ይህ ነው አንድ ሰዉ ከእንቅልፉ ሲነቃ ይህንና ያንን
አለምሁ ካለ በኃላ ሌላ ህልም ለማለም ተመልሶ የሚተኛ ከሆነ ከቅዠት ያለፈ ኑሮ የለውም።እንዲሁም አንድ ሰው
ቀን ቁጭ ብሎ በአይነ ህሊናው እየበረረ ይህንና ያንን ሊያደርግ ራሱን የማየት ልማድ ቢኖረውና ይህ ውስጡ
የሚጓጓለት ነገር በወረቀት ሊጽፍ እቅድ ሊያወጣለትና ከአንድ ደረጃ ወደሌላኛው ደረጃ የማይንቀሳቀስ ካልሆነ ይህ
ሰው ከድንዛዜ አያልፍም።አንድ ነገር ወደ ጋሃዱ ዓለም ከመምጣቱ በፊት በመ መሪያ በጽንሱ ሃሳብ ግን ሊጨበጥና
ሊደረስበት የሚችለው ሲታቀድበትና ስንንቀሳቀስበት መሆኑን አንዘንጋ ከማንም ያልተበደርከውን አንድን በውስጥህ
የበቀለ ጽኑ ፍላጎት ለይተህ እወቀው ከዚያም ፍላጎት አንጻር እቅድን በማውጣት የመ መሪያውን እርምጃ ተራመድ
ብዙ ሳትቆይ ሁኔታህ ሲለወጥ ማየትህ የማይቀር ነው።
በአሁኑ ሰዓት ብዙዎች ስልጣን ላይ ያሉ መዝባሪዎች ዘላቂ የኢትዮጵያን ጥቅም ፋላጊ እንጂ፣ዘላቂ የኢትዮጵያ
ወዳጅ አይደሉም።ለአማራው ምንታዌ እንደማይጠቅመው ያውቃል ኢትዮጵያ አንድነት እንጂ የኢትዮጵያዊ
ምስጢር በአንድነት ገላጭነት ካልታወቀ በስተቀር መረዳት አይቻልም።የስልጣንና የገንዘብ ሌላው አዕይንተ
አዕምሮቸውን በስግብግብነት መንጦላት ጋርዶ፣ዕዝነ ልቡናቸውን በአልጠገብ ባይነት ቡሽ ደፍኖ፣እግሮቻቸውን
በምኞት ፈረስ ከኢትዮጵያዊነት አንድነት ለይተዉ ለወያኔ ተገዥነት እራሳቸዉን አሳልፈዉ ሰጥተው ኢትዮጵያዊነት
ሲሉን እንዴት ነው በእኛ ውስጥ ታአማኒነት ሊኖራቸው የሚችለው።ስልጣንና ገንዘብን መውደድ የክፋት ሁሉ ስር
ነው የሚለው ቃል ተቀይሮ ስልጣንና ገንዘብ የደም ስር ነው በሚለው ብሂል ከተተካ ውሎ አድሯል።ዛሬ በ ገራችን
ኢትዮጵያ ከስልጣንና ገንዘብ ከመውደድ የተነሳ ነፍስ ሲጠፋ፣እውነት ተደብቆ ሐሰት ሲነግሥ ማየት አዲስ ነገር
አይደለም።የስልጣንና የገንዘብ ፍቅር ያነሆለለው ሰው ስለ ኢትዮጵያዊ አንድነት ነገር የሚያስብበት ጊዜ አለው ብዬ
እምነት የለኝም።የድሮ አባቶቻችን ሁለመናቸውን ለሕዝብ ክብርና ለ ገር ፍቅር ሰጥተው የሕዝብን እሮሮ
አድማጭና ተግባሪ የሆኑ መሪዎች የበቀለባት በኢትዮዽያ የታሪክ ገጾች ላይ ሰፍሮ ይገኛሉ።
የኢትዮጵያን ሕዝብን እስከ መቼ ማታለል ይቻላል ኦህዴድና ብአዴን የህወሓት ሞግዚቶች ናቸው እንጂ ምንም
ሊያመጡ አይችሉም።ከሞግዚትነት ወደ ኢትዮጵያዊነት ለመምጣት ማሰባቸው ባይከፋም ነገር ግን እነሱ
እራሳቸውን ከህወሓት አግልለው ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጎራ ሆነው አረንጓዴ፣ቢጫ፣ቀይ ሰንደቅ ባንዲራችንን ለብሰው
እስካልቆሙ ድረስ የሕዝባዊ አመጹን ለማዳከም የሚያደርጉት ሴራ ጉዞአችን መራራ ግብአችንን ዕሩቅ
አያደርገውም።ሮበርት ሙጋቤ ጊዜ ነው እንጂ ቁም ነገራም፣ኖርኩኝስ ማለት አያኮራም ሲል አልሰሙትም
እንዴ።ማንም የህወሓት አሽከር እንዲህ ነው እንዲያ ነው ሲለን ለውጥ ይመጣል ብለን ካሰብን ማስተዋል ተስኖናል
ማለት ነው።ውኃ ተመልሶ ወደ ኃላው ቢሄድ(ቢፈስ) ዎፎች አለ ክንፍ ቢበሩ፣ቁራ እንደበረዶ ቢነጣ ህወሓት አዋቂ
ሊሆን እንደማይችል ጠማማነቱን ቢተው ነብር ዥንጉርጉርነቱን ቢለቅ ህወሓት ክፋታቸውን አይተውም።ስለዚህ
ማስተዋል እኮ የራቀውን ለማቅረብ የቀረበውን ለማራቅ የሚያገለግል የልብ መነጽር ነው።ይህ ትግል ፋና ወጊ በሆነ
ስር የሰደደ ተሞክሮና ለ27 ዓመት በኢትዮጵያ ሕዝብ በደረሰባቸው ስቃይ የተቀሰቀሰ በሕይወት የመኖር መብት
ብሎም የወያኔ ግባተ መሬት የስርዓት ለውጥ ትግል ነው።
የወያኔ አምባገነን አገዛዝ በኢትዮጵያ ሕዝብ ትግል ይወገዳል!!